Saturday, May 14, 2016

ዳዊት ለቦብ ጊልዶፍ ብንቀጥንም ጠጅ መሆናችንን

https://www.youtube.com/watch?v=5TsqJvWqT5k

ዳዊት ለቦብ ጊልዶፍ ብንቀጥንም ጠጅ መሆናችንን

    ጂዮርጂስን! የሻለቃ ዳዊት ወልደጂዮርጂስን ከከፍተኛ ትምህርት፣ ከረጅም ጊዜ ብሔራዊና አለማቀፍ አገልግሎት ከተገኘ ተሞክሮ የመነጨውን ለኢትዮጲያውያን በሙሉ፤ በተለይም ለገዢዎቻችን የተሰጠውን ጥብቅ ማሳሳቢያና ጥልቅ ትንታኔ ስሰማ አንድ ስጋትም አብሮ አደረብኝ።

    ሻለቃ ዳዊት እንደሚሉት በአፍሪካ ላይ ጥናት የሚያደርገው ተቋማቸው ከማንኛውም የአፍሪካ አገር መንግስት ተጽእኖ ነፃ የሆነና በምርምር ያገኘውን መረጃና አስተያዬት ለሚመለከታቸው አገሮች ያለፍርሃትና ያለአድልዎ እንደሚያቀርብ ነው ያስረዱን። እንደምናውቀው ደግሞ አብዛኞቹ የአፍሪካ ገዥዎች ይህን አይወዱም፤ በተለይም የራሳቸው ቀለም ካለው ሰው ትችቱ ሲመጣ እንደ ቆሰለ አውሬ ይሆናሉ። ወያኔ ከሁሉም የባሰ እንደሆነ ደግሞ አንዘነጋውም። እና ለዚህ ስራ አፍሪቃ ሲዘዋወሩ በተለይ መናጢዎቹ ወያኔዎች ከሌሎች ወሮበላ የአፍሪቃ ግብራበሮቻቸው ጋር ተመሳጥረው አደጋ እንዳይጥሉባቸው ሰጋሁ። ይሁንና ተስፋ አደርጋለሁ ሻለቃም ከዚህ አንጻር በቀድሞ የውትድርና ስልጠናቸው ያላንዳች ቸልተኝነት ከባቢያቸውን በንቃት እያዩ ራሳቸውን እንደሚጠብቁ።

       ይህን ካልኩ በኋላ "ገና መሆኑን ያውቃሉ ወይ (Do they know it’s Christmas)?” ብሎ በደፋር ያላዋቂ አንደበቱ የዘፈነውን ቦብ ጊልዶፍን ምንም ብንቀጥን ጠጅ መሆናችንን፤ ደርሰን ለማኝ የሆን ድሃ ብንሆንም ገና ፈረንጅ ዋሻ ውስጥ የሚኖር አረመኔ ሳለ ጀምሮ የኮራ የደራ ባህል ያለን፣ የነበረን መሆኑን እንዲያውቅ ሻለቃ ዳዊት የአይሪሹን ዘፋኝ ያስተማሩበት መንገድ እጅግ የሚመስጥ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እስዎም ያዳምጡት! https://www.youtube.com/watch?v=5TsqJvWqT5k 

No comments:

Post a Comment